የሰብል አርሶ አደሮች ንቦችን ማርባት አለባቸው፡፡ ለምን ካሉ እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች ማወቅ አለብን፡፡


Bees pollinating flowers
የሰብል አርሶ አደሮች ንቦችን ማርባት አለባቸው፡፡ ለምን ካሉ እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች ማወቅ አለብን፡፡

አዲሱ ቢሆነኝ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም

የአበባ ዘር አዳቃይ ነፍሳት ከምንመገበው ምግብ በተጨማሪ አየርን የሚያፀዱ፣ አፈርን የሚያረጋጉ፣ ከከባድ የአየር ሁኔታ የሚከላከሉ እና ሌሎች የዱር እንስሳትን የሚደግፉ ጤናማ ሥነ ምህዳሮች እንዲኖሩ ያግዛሉ፡፡

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ በአበባ አዳቃይ ነፍሳት በተለይም በንቦች ላይ ጥገኛ የሆነው የግብርና ምርት መጠን ወደ 300 በመቶ ገደማ አድጓል፡፡

በዓለም ዙሪያ ካሉ አራት ሰብሎች መካከል ሦስቱ ለሰው ልጅ ለምግብነት አገልግሎት የሚውሉ ፍራፍሬዎችን ወይም ዘሮችን የሚያመርቱ ሲሆን ቢያንስ በከፊል በንቦች ላይ ጥገኛ ናቸው፡፡ የአበባ ዘር አዳቃይ ነፍሳትን (በተለይም ንቦችን) ብዛት እና ብዝሃነትን ማሻሻል የሰብል ምርትን ያሳድጋል፡፡ የአበባ ዘር አዳቃይ ነፍሳት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙት የምግብ ሰብሎች 35 ከመቶው የምግብ ሰብሎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡ 
እኛ የምንበላቸውን በብዙ ጥቃቅን ንጥረ-ምግቦች የበለፀጉ ፍራፍሬዎችን፣ አትክልቶችን፣ የቅባት እህሎች፣ እና ሌሎች ዘሮችን ለማምረት የአበባ ዘር አዳቃዮች በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነገር ግን በሰብል አበባ ማዳቀል አገልግሎቶች ላይ ቀስ በቀስ ያለማቋረጥ ማሽቆልቆል እየታየ ነው። ቀደም ባሉት ጊዜያት ይህ አገልግሎት በተፈጥሮ ያለምንም ክፍያ ይቀርብ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን የእርሻ ማሳዎች ሰፋፊ ሆነዋል፣ የግብርና ልምዶችም እንዲሁ በውስን ሰብሎች እና በኬሚካሎች አጠቃቀም ላይ በማተኮር ተለውጧል፡፡ 
በእርግጥ ለሰው ልጅ ፍጆታ ፍራፍሬዎችን እና ዘሮችን ከሚያመርቱ የአለም ሰብሎች ወደ 75 ከመቶው የሚጠጋው ቢያንስ በከፊል ለምርት ቀጣይነት፣ ምርት ብዛት እና ጥራት ሲባል በአበባ ዘር አዳቃይ ንቦች ላይ ጥገኛ ነው፡፡ የሚቀርበው ብዝሃ-ምግብ በአብዛኛው የእነዚህ አዳቃዮች ዕዳ ነው፡፡ 
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ለአበባ ዘር አዳቃዮች፣ በተለይም ለንቦች በከፍተኛ የከፋ ማሽቆልቆል መንስኤ ናቸው፡፡ ማሽቆልቆሉ ቀድሞውኑ በሰብል ምርት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ እና በቫይታሚን የበለፀጉ ሰብሎች እንደ ፍራፍሬና አትክልት ወጭዎች ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ያልተመጣጠኑ አመጋገቦች እንዲሁም እንደ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያሉ የጤና እክሎችን ያስከትላል፡፡ 
 የ2018 የምግብ እና እርሻ ድርጅት ሪፖርት ‘ንቦች እና ሌሎች የአበባ ዘር አዳቃዮች ለምግብ እና ለግብርና አስፈላጊነት’ በሚል ርዕስ የአበባ ዘር ማዳቀልን (pollination) በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ምርት ለማግኘት ጉልህ የግብርና አስተዋፅዖ አበርክቷል፡፡ ስለሆነም ንቦች እና ሌሎች የአበባ ዘር አዳቃዮች ለግብርና አስፈላጊ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡ 
 እንደ አለመታደል ሆኖ በአብዛኛው የዓለም ክፍሎች ውስጥ የአበባ ዘር ማዳቀል አገልግሎቶች እየቀነሱ ያሉ አዝማሚያዎችን እያሳዩ ነው፡፡ ለምሳሌ በግብርና ልማት ስር በአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎች ውስጥ ምርትን ማቆየት እና መጨመር ለጤና፣ ለምግብ፣ ለምግብ ዋስትና እና ለአነስተኛ አርሶ አደሮች የተሻለ ገቢ አስፈላጊ ነው፡፡ 
 ንቦች የሚሰጡን ጥቅሞች ከሰው ምግብ በላይ ናቸው፡፡ የዱር አዳቃይ ነፍሳትን በሚደግፉ ልምዶች የአበባ ዘር ማዳቀል አገልግሎቶችን እንዲሰጥ በተፈጥሮ ላይ ሆን ተብሎ ሊሰራበት ይገባል፡፡ ያ አሠራር እንደ ማንኛውም እንስሳ ሁሉ ንቦችን ማቆየት ብቻ ነው፡፡ 
 በዓለም ላይ በንብ ውጤቶች ከሚገኘው ገቢ ይልለቅ ንቦች ለእፅዋት የሚያደርጉት የማዳቀል አስተዋፅኦ ግምታዊ ዋጋ ላቅ ያለ መሆኑ አሁናዊ የምርምር ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለሆነም በእነዚህ ሁኔታዎች ሲቃኝ ንብን ማርባት ያለባቸው የሰብል አምራች አርሶ አደሮች መሆን ይገባቸዋል፡፡ ወይም ደግሞ የንብ እርባታውን ዘርፍ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 መልካም ጊዜ! 
 በዘርፉ አዳዲስ ወቅታዊ አስተማሪ መረጃዎች እንዲደርስዎ ከዚህ በታች ያሉትን ሚዲያዎች ይቀላቀሉ ወይም አባል ይሁኑ፡፡ 

ዌብሳይት፡ https://wordpress.com/view/addisubihonegn.wordpress.com

ቴሌግራም፡ https://t.me/semonegna

ፌስቡክ ግሩፕ፡ https://www.facebook.com/groups/514839721862656 
ከወደዱት Like, Comment እና Share ማድረግዎን እንዳይረሱ፡፡ 

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: