የሰውና ጥቃቃን ነፍሳት ግንኙነት፡ ለምድር ዕጣ ፈንታ


የሰው ልጅ የአበባ አዳቃይ ነፍሳትን ጨምሮ በተፈጥሮ ላይ የተመሰረቱ ንብረቶችን የሚያስተዳድርበት መንገድ በ 21ኛው ክፍለዘመን ውስጥ የጋራ የወደፊት ዕድላችንን በከፊል ይገልጻል፡፡ 
በዓለም ውስጥ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የእንስሳት ዝርያዎች እንዳሉ ይታመናል፡፡ ከእነዚህ እንስሳት መካከል 1ሚሊዮን ገደማዎቹ አነስተኛ ነፍሳት ሲሆኑ እነዚህም ተፈጥሮን በተለያየ መንገድ እየጠበቁ ያሉ ናቸው፡፡ ይህም አፈርን በማልማት፣ የተፈጥሮ ጋዝን በማመቅ፣ ሙቀትን በማመጣጠን፣ ብክለትን በመቀነስና በአብዛኛዎቹ ደግሞ የዕፅዋትን አበባ በማዳቀል ህይዎት በምድር ላይ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ሌሎች እንስሳት (በተለይ ሰውን ጨምሮ) ደግሞ በእነዚህ ጥቃቅን ነፍሳት እየተጠበቀች ያለችን ምድር ከነጠባቂዎቻቸው ለማጥፋት ሲተጉ እናያለን፡፡ በተለይ ግብርናን በማዘመን ሂሳብ አግባብ የሌለው ልቅ የኬሚካል አጠቃቀም ይስተዋላል፡፡ ይህ ኬሚካልም ከአዳቃይ ነፍሳት (በተለይ ንቦች) መጥፋት ያልተናነሰ፣ በአፈር ለምነትና ምርታማነት ላይ፣ በውሃና በአየር ብክለት ላይ፣ በእንስሳትና በሰው ልጅ ጤና ላይ፣ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድ ብዙ ብዙ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡  ያ…ማ…ል፡፡ 
በዚህ አያያዝ ምድራችን ህልውናዋ አደጋ ላይ ነው፡፡ 
ስለሆነም የአበባ አዳቃይ ነፍሳትን ህልውና መጠበቅ ምድራችንን ከጥፋት፣ ራሳችንንም ከህልፈት መታደግ ነውና እናስብበት የሚለው የዛሬውና የዘወትር መልዕክቴ ነው፡፡
ጀመርኩ… አላበቃሁም…  

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: