ሰው ሰራሽ ክህሎት፣ የነገሮች በይነመረብ እና ትልቅ መረጃ ንቦችን ማዳን እንዴት እንደሚችል


Bernard Marr            Contributor        Enterprise Tech

ዘመናዊ ግብርና በንቦች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በእውነቱ፣ የምንበላው ምግብ እና የምንተነፍሰው አየርን ጨምሮ አጠቃላይ ሥነ-ምህዳራችን አዳቃይ ነፍሳት ላይ ይመሰረታል፡፡ የአለም ንብ ፕሮጀክት መስራች እና ስራ አስፈፃሚ ፕሬዝዳንት ሳቢሃ ሩማኒ ማሊክ እንደሚሉት ግን የእነዚህ አዳቃይ ነፍሳት ብዛት እየቀነሰ ነው፡፡ ግን ከኦራክል ጋር በሚያስደንቅ ትብብር እና ሰው ሰራሽ ክህሎት፣ የነገሮች በይነመረብ እና ትልቅ መረጃ በችግሩ ላይ እንዲሰሩ በማድረግ አዝማሚያውን ለመቀልበስ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡

የዓለም ንብ ቁጥር ለምን እየቀነሰ መጣ?

በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ ፖሊሲ መድረክ (IPBES) ላይ በብዝሃ ሕይወት እና ስነምህዳር አገልግሎቶች ሪፖርት እንደተመለከተው የአበባ ዘር  አዳቃይ ነፍሳት አደጋ ላይ ናቸው፡፡
የአበባ ዘር አዳቃይ ነፍሳት ወደ መጥፋት የሚሄዱባቸው የመኖሪያ አከባቢ መጥፋት፣ የከተማ መስፋፋት፣ ፀረ-ተባዮች አጠቃቀም፣ ብክለት፣ የተፈጥሮ የአበባ መኖሪያዎች መበታተን፣ አዳኞች እና ጥገኛ ተውሳኮች እና የአየር ንብረት መለዋወጥን ጨምሮ ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ሆኖም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአለም ንብ ፕሮጀክት ስራ የንብ ብዛትን ለማጥናት ወይንም ጉዳዩን ከዓለም አቀፉ እይታ አንጻር ለማጥናት እና ምላሽ ለመስጠት ዓለም አቀፍ ተነሳሽነት አልነበረም፡፡

ንቦችን ማዳን ለምን አስፈላጊ ነው?

ንቦች ከሌሎች ለምሳሌ እንደ ቢራቢሮዎች ካሉ አዳቃይ ነፍሳት ጋር የዕፅዋት ዘሮችን ለማፍራት እና ለማባዛት ምክንያት እንደሆኑ ያውቃሉ?
የዩናይትድ ስቴትስ የግብርና መምሪያ (ዩኤስዲኤ) እንደገለጸው 35 ከመቶ የምግብ ሰብሎች እና ሦስት አራተኛ የአበባ እጽዋት ንቦች እና የአበባ አዳቃይ ነፍሳት ላይ ጥገኛ ናቸው፡፡ በእርግጥ በካሊፎርኒያ ውስጥ በየአመቱ የአልሞንድ ሰብል የአበባ ዘር መዳቀሉን ለማረጋገጥ በአሜሪካ ውስጥ የሚገኙት አብዛኛዎቹ ቀፎዎች ወደ ካሊፎርኒያ ይላካሉ፡፡ በእርግጥ ንቦች የፍራፍሬ ዛፎችን፣ ቡናዎችን፣ ቫኒላ እና የጥጥ እፅዋትን ጨምሮ 90% ከሚሆኑት የአለም አቀፍ የሰብል አይነቶችን ለማዳቀል (ለማራባት) ይረዳሉ፡፡ እናም በእርግጥ ጤናማ እፅዋቶች በፎቶሲንቴሲስ ምክንያት የኦክስጂን አቅርቦታችንን ለመሙላት ወሳኝ ናቸው፡፡
የአበባ አዳቃዮች ሥራቸውን ለመፈፀም በሕይወት ከሌሉ ወይም ጤናማ ካልሆኑ የአለም የሰብል ምርታችን፣ የምግብ ዋስትናችን፣ ብዝሃ ህይወታችን እና ንፁህ አየር አደጋ ላይ ነው፡፡ የማር ንቦች በዓለም ላይ በጣም አስፈላጊ የአበባ አዳቃዮች ናቸው፡፡ ለሰው ልጆች ከሚቀርበው የዓለም ንጥረ-ምግብ አቅርቦት ከ40 በመቶው የሚበዛው በንቦች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በግምት 2 ቢሊዮን ሰዎች በማይክሮኤለመንቶች እጥረት የሚሠቃዩ አሉ፡፡
“ህይወታችን ውስጣዊ በሆነ መልኩ ከንቦቹ ጋር የተቆራኘ ነው” ማሊክ እንደተናገረው፡፡

ዓለም አቀፍ የማር ንብ ቁጥርን ለመቆጣጠር የተጀመረ ሽርክና

የዓለም ንብ ፕሮጀክት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ እና የዓለምን የማር ንብ ብዛት ለመከታተል ያተኮሩ የመጀመሪያው የግል ድርጅት ነው፡፡ ከ2014 ጀምሮ ድርጅቱ ስለ አርሶ አደሮች፣ መንግስታት፣ ንብ አናቢዎች እና ሌሎች ተልዕኮ ያላቸው ድርጅቶች ጉዳዩን በተመለከተ ግንዛቤ እንዲሰጣቸው የሳይንስ ሊቃውንት አንድ ላይ በመሰባሰብ ዓለም አቀፍ የንብ ማነስ ችግርን ያጠናሉ፡፡ እ.ኤ.አ. በ2018 የኦራክል ክላውድ ቴክኖሎጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ የንብ ብዛት መቀነስን በተሻለ ለመረዳት ወደ ሥራው የተገባ ሲሆን የአለም ንብ ፕሮጀክት ቀፎ አውታረመረብ (The World Bee Project Hive Network) ተጀመረ፡፡

ቴክኖሎጂ ንቦችን እንዴት ይታደጋቸዋል?

ንቦችን ለማዳን ቴክኖሎጂ እንዴት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል? በሌሎች የፈጠራ ፕሮጄክቶች ላይ በሚተገበር ተመሳሳይ ዘዴ ንቦችን ለማዳን ቴክኖሎጂ ሊመደብ ይችላል፡፡ በመጀመሪያ፣ ወራሪ አዳኞችን ማየት እና ከንቦች እና ከቀፎዎች መረጃ መሰብሰብ የሚችሉ ማይክሮፎኖችን እና ካሜራዎችን ጨምሮ የነገሮችን በይነመረብ ዳሳሾች  መጠቀም፡፡ እንደ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂዎች፣ ሮቦቲክስ እና የኮምፒተር እይታ ያሉ የሰው ብልሃቶች እና ፈጠራዎች ለጉዳዩ አዳዲስ ግንዛቤዎችን እና መፍትሄዎችን ለማድረስ ይረዳሉ፡፡
ከቀፎ ጤንነት ቁልፍ ከሆኑ መለኪያዎች አንዱ የሚያወጣቸው ድምፆች ናቸው፡፡ ለመረጃ አሰባሰብ ጥረቶች ወሳኝ የሆነው የህብረ ንብ ጤናን፣ ጥንካሬን እና ባህሪን ለመለየት እንዲሁም የሙቀት መጠንን፣ እርጥበትን፣ የአየር ንብረትን ሁኔታ እና የቀፎ ክብደትን ለመለየት ቀፎዎችን “ማዳመጥ” ነው፡፡ የድምፅ እና የምስል ዳሳሾች እንዲሁ ለንብ መንጋ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ጠላቶችን መለየት ይችላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ መረጃው ለመተንተን ሰው ሰራሽ ክህሎት (AI) ስልተ ቀመሮች (algorithms) ሥራ ላይ ወደሚውልበት ወደ ኦራክል ደመና (ክላውድ) ይመገባል፡፡
ስልተ ቀመሮቹ (algorithms) ዘይቤዎችን (patterns) ይፈልጉና ለመሰደድ እየተዘጋጀ ያለ የቀፎ ባህሪያትን ለመተንበይ ይሞክራሉ፡፡ ግንዛቤዎቹ ከዚያ ንብ አናቢዎችና የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ጋር ይጋራሉ። ስለዚህ ቀፎዎችን ለመከላከል ለመሞከር ወደ ውስጥ መግባት ይችላሉ፡፡ እሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገናኘ አውታረ መረብ በመሆኑ፣ ስልተ ቀመሮቹ እንዲሁ በተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ውስጥ በሚገኙ የህብረ ንብ ልዩነት የበለጠ ማወቅ ይችላል።
ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና ፍላጎት ያላቸው ዜጎችም እንዲሁ ከመረጃው ጋር መስተጋብር መፍጠር፣ በቀፎው አውታረመረብ ክፍት ኤ.ፒ.አይ አማካኝነት ከእሱ ጋር መሥራት እና በቻትቦት በኩል መወያየት ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፣ የድምፅ እና የምስል ዳሳሾች የንብ ጠላቶችን መለየት ይችላሉ፣ ይህም ለንብ መንጋ ስጋት ሊሆን ይችላል፡፡
ከንብ ጠላት የክንፍ እርግብግቢት ወይም የሚሰማው ድምፅ ከንቦች የተለየ ነው፣ እናም AI ይህንን በራስ-ሰር ማንሳት እና የንብ አናቢዎችን ስለ ንብ ጠላት ስጋት ማስጠንቀቅ ይችላል፡፡ የአለም ንብ ብዛትን ለማዳን የሚረዳ የእውነተኛ ጊዜ መረጃን ለማካፈል እና ሀብቶችን ለማሰባሰብ ቴክኖሎጂ ለዓለም ንብ ፕሮጀክት ቀላል እየሆነለት ነው፡፡ በእርግጥ ማሊክ “ከኦራክል ደመና ጋር ያለን አጋርነት በተፈጥሮ እና በቴክኖሎጂ መካከል ያልተለመደ ጋብቻ ነው” ሲል አጋርቷል፡፡ ቴክኖሎጂው የአለም ንብ ፕሮጀክት ቀፎ አውታረ መረብን ተፅእኖ በመላው ዓለም ለማባዛት እየረዳ ሲሆን ንቦችን በፍጥነት እና ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማዳን እርምጃ ይወስዳል፡፡
ምንጭ፡- ፎርብስ መፅሄት https://www.forbes.com/sites/bernardmarr/2020/04/22/how-artificial-intelligence-iot-and-big-data-can-save-the-bees/?sh=7cbf1f201d9e
አዳዲስ ወቅታዊ አስተማሪ መረጃዎች እንዲደረስዎ
https://wordpress.com/view/addisubihonegn.wordpress.com
https://t.me/semonegna

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: