የማር ንቦች አስተዋፅኦ ለሰብል የአበባ ዘር ልማት፣ ለምግብ ዋስትና እና ለኢኮኖሚ መረጋጋት በኢትዮጵያ


Fikadu, Z. (2020). The Contribution of Managed Honey Bees to Crop Pollination, Food Security, and Economic Stability: Case of Ethiopia. The Open Agriculture Journal, 13(1), 175–181. https://doi.org/10.2174/1874331501913010175  
Honeybee and Pollination
ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ ሁኔታ የማር ንቦች የአበባ ማዳቀል (የአበባ ዘር ልማት)አገልግሎት ለግብርና ሰብሎች እና ለምግብ ዋስትና ያለውን ሚና እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ይገመግማል፡፡ የማር ንቦች ለዘር ማዳቀል እና የበርካታ የግብርና ሰብሎችን ጥራት እና ብዛት ለማሻሻል በጣም አስፈላጊ የሆኑ የአበባ ዘር ልማት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ 
በኢትዮጵያ ከተመረቱት ጉልህ 53 ሰብሎች ውስጥ 33 (62.2%) ስነይወታዊ አዳቃዮች ላይ ጥገኛ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የማር ንቦች ወሳኝ ኢኮኖሚያዊ ሚና ያላቸው ሲሆን በግብርና ሰብሎች ላይ የአበባ ዘር ልማት አገልግሎት መስጠታቸው በኢትዮጵያ ወደ 815 ሚሊዮን ዶላር ያህል ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ አስተዋጽኦ በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ዘንድ አይስተዋልም፡፡
የማር ንብ የአበባ ዘር ልማት አገልግሎት በሰው ልጅ አመጋገብ፣ የምግብ ዋስትና አቅርቦት፣ የቤተሰብ ገቢ እና ሥነ ምህዳር የማሻሻል አገልግሎቶች ላይ ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ በመላው ዓለም የማር ንቦችን ጨምሮ በአዳቃይ ነፍሳት ማሽቆልቆል የተነሳ የአበባ ዘር ልማት አገልግሎት አቅርቦት ለግብርና ዘርፍ ትልቅ ሥጋት ፈጥሯል፣ ምክንያቱም አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት የግብርና ምርቶች አዳቃይ ነፍሳት በዋናነት በማር ንቦች ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ነው፡፡
ለንብ መንጋዎች ማሽቆልቆል መንስኤ ከሆኑት በርካታ ምክንያቶች መካከል ተገቢ ያልሆነ ፀረ-ተባዮች አጠቃቀም እና የአየር ንብረት ለውጥ ዋና ዋናዎቹ እና ለአደጋ ያጋለጡ ናቸው፡፡ የንብ መንጋ ማሽቆልቆል ሊያስከትል የሚችላቸው መጥፎ ውጤቶች ውስጥ በሰብሎች መቀነስ ምክንያት የሚከሰቱ ቀጥተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራዎችን እንዲሁም በስነ-ምህዳሩ ውስጥ ያለው ዝቅተኛ ምርታማነት ምክንያት በግብርናው እንቅስቃሴ ላይ ሰፊ ተጽዕኖ ማሳደር ይገኙበታል፡፡ በኢትዮጵያ የንቦችን የአበባ ዘር ልማት አገልግሎት በማስተዋወቅና እንደ ግብርና ልማት ፓኬጅ በመጠቀም የንብ ልማትን እና የሰብል ምርትን ማሻሻል ይቻላል፡፡

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: