የንብ አረባብ ዘዴ እና የንብ ውጤቶች በህብረ-ንቦች ላይ የሚያሳድሩት የሙቀት ተፅዕኖዎች በጥናት ተረጋገጠ


የንብ አረባብ ዘዴ እና የንብ ውጤቶች በህብረ-ንቦች ላይ የሚያሳድሩት የሙቀት ተፅዕኖዎች

Daniel Cook, Alethea Blackler, James McGree, Caroline Hauxwell

በ1854 (እ.ኤ.አ) ላንግስትሮዝን የሚንቀሳቀስ ባለፍሬም ቀፎ ዲዛይንና የማዘመን ሥራ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የቀፎ ዲዛይንና የንብ ማነብ ሂደቶች በመሠረቱ አልተለወጡም፡፡

የአፒስ ሜሊፌራ ሊኔስ ህብረ-ንቦች (ሂሚንቶፕቴራ አፒዴ) (የማር ንብ) ለዕጭ ዕድገት ወሳኝ በሆነው ከ 34.5 – 35.5°ሴ ባለው ጠባብ የሙቀት ክልል ውስጥ ያለውን የቀፎ ሙቀት መጠን ይጠብቃሉ፡፡

ንቦች የቀፎ አከባቢን ማሻሻያ በማድረግ የቀፎው ሙቀት ተፈላጊና ተመጣጣኝ ላይ ለማቆየት ከፍተኛ ኃይልን ያወጣሉ፡፡

የሰው ልጅ የማር መሰብሰብ ሂደቶች እና በማር የተሞላው ሰም (የሙቀት መጠን ምንጭ) መወገድ በቀፎው የሙቀት መጠን ላይ የኃይል መጨመርን የሚጠይቅ መጥፎ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡

በንቦቹ ላይ ያለው ይህ ተጨማሪ የኃይል ፍላጎት በህብረ-ንቦቹ ላይ ተጨማሪ ሥራ (የጭንቀት ዓይነት) ሲሆን ሠራተኛ ንቦችን ከሌሎች አስፈላጊ ሥራዎች ይልቅ ወደ አካባቢያዊ ሙቀት አስተዳደር ያዞራል፡፡  

የማር መወገድ እና ማውጣት ያስከተለውን የሙቀት ኃይል ብክነት፣ የአውስትራሊያ መደበኛ ላንግስትሮዝ ባለ 10 ፍሬም ቀፎ የሙቀት መጥፋት መጠን፣ እንዲሁም ባልተያዘ የንብ ቀፎ ውስጥ የማር እና የሰም ውጤት እንደ ሙቀት ሰጪ አካል መርምረናል፡፡  

ውጤቶቹ እንደሚያሳዩት ከማር ማምረት ወይም ፍሬም ከተጨመረ በኋላ የቀፎው አከባቢን ሙቀት ለማስተካከል ከፍተኛ የኃይል ወጪ ያስፈልጋል፡፡  

ማር ከላንግስትሮዝ ቀፎ ቀለል ካለው ዲዛይን የተነሳ ለውጫዊ የሙቀት ለውጥ እንደ የሙቀት ቋት ሆኖ የሚሠራ፣ የሙቀት ኪሳራዎችን በከፊል ሊያስታርቅ የሚችል የቀፎ ውስጥ የሙቀት አማቂ ሃይልን ይሰጣል፡፡  

አሁን ባለው የንብ አረባብ ባህል እና የቀፎ ዲዛይን የእነዚህን ተጽዕኖዎች መለየት የንብ ቀፎዎችን እና ተጓዳኝ አሠራሮችን ንድፍ ለማሻሻል ይረዳል፡፡  

እነዚህ ማሻሻያዎች ለህብረ-ንቡ የአበባ ማዳቀል ተግባርና የአበባ የመሰብሰብ ቅልጥፍናን በመጨመር በንብ መንጋ ላይ የሥራ ጫናን ሊቀንሱ ይችላሉ፡፡

ሙሉ የጥናቱን ፅሁፍ በዚህ ሊንክ ያገኙታል፡፡

Publisher URL: https://academic.oup.com/jee/article/114/2/538/6168215

Unpaywall URL: https://academic.oup.com/jee/advance-article-pdf/doi/10.1093/jee/toab023/36549547/toab023.pdf

DOI: https://doi.org/10.1093/jee/toab023

ለተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎች www.addisubihonegn@wordpress.com ይጎብኙ ወይም https://t.me/semonegna ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: