የሰም እንጀራ ዕድሜ የንብ (አፒስ መሊፌራ) መንጋ ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አንድ ጥናት አመለከተ፡፡


የሰም እንጀራ ዕድሜ የንብ (አፒስ መሊፌራ) መንጋ ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል

EKA Taha, OM Rakha, ESM Elnabawy, MM Hassan, DMB Shawer

Journal of King Saud University-Science

የጥናቱ ዓላማዎች

ንቦች በዋናነት የሰም እንጀራ ለመራቢያ እና ምግብ ማከማቻነት ይጠቀሙበታል፡፡  በተደጋጋሚ ዕጭ በሚፈለፈልበት ወቅት የሰም እንጀራው ቀለም ይቀየራል፤ እንዲሁም የአይነበጎ መጠን ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ የዚህ ጥናት ዓላማ የሰም እንጀራ ዕድሜ የንቦች የሰውነት መጠን መቀነስንና በህብረ-ንቦች ምርታማነት አቅም ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ማጥናት ነው፡፡ 

የጥናት ዘዴ

እያንዳንዳቸው 12000 ንቦች ሃያ የተዳቀሉ የካርኒዮላን ​​ህብረ-ንቦች ጥቅም ላይ ውለው ነበር፡፡ ከ1-3 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የማር እንጀራዎች እንደ አዲስ እንጀራዎች ፣ እና ከ4-6 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የሰም እንጀራዎች እንደ አሮጌ እንጀራዎች ያገለግሉ ነበር፡፡ የሰራተኛ ፣ ንግስት ፣ ድንጉላ  ክብደት እና የንብ ወተት (ሮል ጀሊ)፣ የንግስት አርኬና ፣ የአበባ ዱቄትና ማር ማከማቸት እና የሰራተኛ እና የድንጉላ አስተዳደግ መረጃ ተወስዷል ፡፡

ውጤት

እንደ ማጠቃለያ: በአዲስ የሰም እንጀራ ላይ አዲስ የሚፈለፈሉ ሰራተኛ፣ ድንጉላና ንግስት ንቦች የሰውነት ክብደት እንዲሁም ተንከባካቢና ቀሳሚ ሰራተኛ ንቦች ከአሮጌ እንጀራ ላይ ከተገኙት ይልቅ ከፍተኛ ክብደት ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡  በአዲስ እንጀራ ላይ ያሉ ህብረ-ንቦች ከአሮጌ እንጀራ ላይ ከተገኙት ይልቅ የንብ ዳቦ (ፅጌ ብናኝ) እና ማርን በመሰብሰብ፣ የንብ ወተትን በማምረት፣ ሰራተኛና ድንጉላ ንብን በመንከባከብ በኩል የበለጠ ንቁ ነበሩ፡፡ ከጥናቱ ማጠቃለል እንደተቻለው የእያንዳንዳቸው ንቦች የሰውነት መጠን እና የህብረ-ንቡ ምርታማነት በሰም እንጀራ ዕድሜ መጨመር ምክንያት እየቀነሰ እንደሚሄድ ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡  የህብረ-ንቡን ዕድገት ለማበረታታትና ምርታማነትን ለመጨመር የማር እንጀራን በየሦስት ዓመቱ በአዲስ መተካት ይመከራል፡፡  

ሙሉ የጥናቱን ፅሁፍ በዚህ ሊንክ ያገኙታል፡፡ https://www.sciencedirect.com/science/article/pii/S1018364721000975

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: