የንብ እርባታ ምንነትና ጠቀሜታው (ክፍል አንድ)


ሰላም የዚህ ቡድን አባላትና ተከታታዮች እንደምን አላችሁ? እንዴት ከረማችሁ?

ሰላማችሁ ይብዛና ቀደም ሲል በዚህ ቡድን የተለያዩ አዳዲስ መረጃዎችን ከተገኙበት የመረጃ ምንጭ በቀጥታ በማስተላለፍ (ሊንክ ፖስት) ቆይተናል፡፡

ከዚህ በኋላ ከዚህ በፊት በተለመደው ከምናቀርበው በተጨማሪ በተከታታይ ለአናቢዎች፣ ለልማት ጣቢያ ሰራተኞች፣ በአጠቃላይ በንብ እርባታ ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ ሁሉ መረጃ እንዲሰጥ፣ እንዲያስተምርና የሥራ መነሻ መመሪያ የሚሆን ታስቦ በአማርኛ የተዘጋጀ ሰፊ ዝግጅት እናቀርባለን፡፡ ዝግጅቱ የሚያካትታቸው ርዕሰ ጉዳዮችም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡

 • ስለንብ እርባታ ምንነትና ጠቀሜታው
 • ንብ ለማርባት ወይም ለማነብ ምን ምን ሁኔታዎች መሟላት አለበት? እንዴት መጀመር እንችላለን?
 • የንብ እርባታ በኢትዮጵያ ምን ይመስላል ወይም በምን ደረጃ ላይ አለ? ያሉ ተግዳሮቶች ወይም እስካሁን በዘርፉ ለምን አልተጠቀምንም?
 • የንብ ስነ-ፍጥረት ወይም ስነ-ህይወት እና የእያንዳንዳቸው የንብ ቤተሰቦች የሥራ ድርሻ ምን ይመስላል?
 • ህብረ-ንቦችን ማባዛት በምን ሁኔታ፣ መቼና እንዴት ይቻላል?
 • የህብረ-ንብ ዝር ማሻሻል እንዴት ይቻላል?
 • የዘወትርና ወቅታዊ የንብ እርባታ ሥራዎች ምን ምን ናቸው?
 • የንብ ውጤቶች የሚባሉት ምን ምን ናቸው? ጠቀሜታቸው፣ የአመራረት ሂደት፣ የጥራት አጠባበቅ፣ አያያዝ፣ የእሴት ጭማሪና ግብይት ምን መሆን አለበት?  
 • የንብ ጤናን በተመለከተ በተለይም ስለንብ በሽታ፣ ስለንብ ጠላቶች፣ ስለመርዛማ ዕፅዋትና የግብርና ኬሚካል በንቦች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖና መፍትሄዎች ዙሪያ
 • ተፈጥሯዊ የንብ እርባታ መርሆችና ልንከተላቸው የሚገቡ ዓለም አቀፍ ህጎች
 • የመረጃ አያያዝ እና ሌሎችም ወሳኝ የንብ እርባታ ርዕሶችን እያነሳን እንማማራለን፣ እንወያያለን፡፡

በሁሉም ርዕሶች ላይ አለምአቀፍ ተሞክሮዎችንም በማንሳት፣ ጥልቅና ተከታታይ ትንታኔ በመስጠት ለረጅም ጊዜያት አብረን እንቀጥላለን፡፡

ወደፊት በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛዎች (ለምሳሌ በፌስቡክ ቀጥታ ስርጭትና በዩቲዩብ) ለመምጣት ሃሳብ አለን፡፡ ለጊዜው ግን የፌስ ቡክ ግሩፑ (የቡድኑ) https://www.facebook.com/groups/514839721862656 አባል በመሆን ወይም በቴሌግራም ቻናል https://t.me/semonegna በትዊተር ገፅ https://twitter.com/AddisuBihonegn ወይም በቀጥታ ከዌብሳይታችን https://addisubihonegn.wordpress.com/ መከታተል ትችላላችሁ፡፡

ለዛሬ በባዶ እንዳንለያይ ንብ ማርባት ለምን አስፈለገ የሚለውን በአጭሩ እናነሳለን፡፡

የሰው ልጅ ንቦችንና ውጤታቸውን ለራሱ ጥቅም ያዋለበት ጊዜ በውል የሚታወቅ ባይሆንም፡፡

ንቦች በተፈጥሮ ሃብት ላይ ጥገኛ ከመሆናቸው የተነሳ በጫካ፣ በዋሻዎች፣ ለሌሎች እንስሳት ምቹ ባልሆኑ ቦታዎች መኖሪያቸውን በመስራት፣ ጥሩ የቀሰም ዕፅዋት ስብጥር በሚገኝበት አካባቢ ምግባቸውን ከአበባዎች በማዘጋጀት የሚኖሩ ትንንሽ ፍጥረታት ናቸው፡፡ የሰው ልጅም ከዘመናት በፊት ለራሱ እንዲመቸው፣ እንዲቀርበውና እንዲጠቀምባቸው ሲል ንቦችን መቆጣጠርና ማርባት ጀመረ፡፡ ስለሆነም ንብ እርባታ ማለት የንብ ውጤቶችን ለሰው ልጅ ጥቅም እንዲውል የማድረግ ጥበብና ሳይንስ ነው፡፡

ንብ ማነብ ለምን ይጠቅማል?

አንድን ሥራ ከመጀመራችን ወይም ወደዘርፉ ከመግባታችን በፊት ስለጠቀሜታዎቹ በተለይም አንፃራዊ ጠቀሜታው ከሌሎች የተሻለና አዋጭ መሆኑን መረዳት ይጠበቅብናል፡፡ በንብ እርባታም ለመሰማራት ካሰብን እንዲሁ ማወቅ ያለብንን ሁሉ በውል ተረድተን መሆን ይገባዋል፡፡

ንብ ማነብ ለምን ይጠቅማል ብንባል ብዙዎቻችን ለማር ምርት፣ ከማር በሚገኝ ገንዘብ ለመጠቀም ከሚሉ ጥቂት ጠቀሜታዎች ውጪ ብዙም ስንጠቅስ አንታይም፡፡ ምክንያቱም በታዳጊ ሃገራት የንብ እርባታ ከማር ማምረት የዘለለ ጠቀሜታ ሲሰጥ አልታየም፡፡ በተወሰነ መልክ ሰም እንደሁለተኛ ምርት ተደርጎም ቢሆን (ማሩ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ እንደተረፈ ምርት ማለት ነው) እፎ አልፎ ጥቅም ሲሰጥ ይታያል፡፡ ነገር ግን የንብ ጠቀሜታ ከዚህ ላቅ ያለ የሰው ልጅ ህልውና መሰረት የሆኑ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ እነዚንም ጠቀሜታዎች በሦስት ዘርፎች ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ አንደኛው ዘርፍ ላይ ያየነው ጠቀሜታ ሌላው ላይ ሊደገም ይችላል፡፡ ነገር ግን ዘርፎችን ለማጠናከር እንዲቻል ነው፡፡

 1. እንደማንኛውም የግብርና ዘርፍ አጠቃላይ ጠቀሜታው
 2. ልዩ ልዩ ጠቀሜታዎች (ቤተሰባዊ፣ ለሃገራዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ ማኅበራዊ ፋይዳ)
 3. አንፃራዊ ጠቀሜታዎች (ከሌሎች የስራ ዘርፎች በተለይም ሰብል ማምረት፣ እንስሳት እርባታ ከመሳሰሉ የግብርና ዘርፎች አንፃር ያለው  ተቀሜታ)

በሚቀጥለው እያንዳንዳቸውን ጠቀሜታዎች በዝርዝር ይዤ እመለሳለሁ፡፡

ላይክ፣ ሼር፣ በማድረግ እንዲሁም ተጠቃሚ መሆን አለባቸው የምትሏቸውን እዲቀላቀሉ በመጠቆም (suggest በማድረግ) የተጠቃሚውን አባል ቁጥር እንድታሳድጉ እንዲሁም ወደፊት ምን መስተካከልና መካተት እንዳለባቸው አስተያየት በመስጠት እንድትተባበሩን ትጠየቃላችሁ፡፡

መልካም ጊዜ!

በሰላም እንገናኛለን!!

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: