የሰኔ 14ቱ የፀሃይ ግርዶሽን እንዴት በቀላሉ መመልከት እንችላለን!


ሰላም የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን እንደምን አላችሁ የፀሀይ ግርዶሽን በአካባቢ በሚገኝ ቁሳቁስ እንዴት እንደሚሰራ አሳያችኋለሁ፡፡

የፀሃይ ግርዶሽ ማለት ጨረቃ በመሬትና በፀሃይ መካከል ሆና የፀሃይ ብርሃን ወደ መሬት እንዳይደርስ በከፊል ወይም በሙሉ የምትሸፍንበር ክስተት ሲሆን ይህ ክስተት በዘመናት መካከል የሚታይ ነው፡፡

ሙሉ ወይም ቶታል የጸሃይ ግርዶሽ በየ3 ዓመት ሁለት (2) ጊዜ ሲከሰት፣ በአንድ ስፍራ ላይ በድጋሚ ለመከሰት እስከ 400 ዓመት ሊፈጅ ይችላል። ከዚህ በኃላ በሀገራችን ብዙ ሰዎች የሚመለከቱት ከሰኔ 14ቱ ጋር ተመሳሳይ ግርዶሽ የሚከሰተው ከ54 ዓመት በኃላ ሲሆን የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ ክስተቱ ወለጋ አካባቢ ጀምሮ ከፊል ጎጃምን፣ ከፊል ጎንደርን አልፎ ወደ ወሎ ላሊበላን አቋርጦ ይሄዳል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ፀሐይ እስከ 99 ፐርሰንት ተሸፍና ቀለበታዊውን ግርዶሽ ማየት ይቻላል፡፡

እሳታማ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ ማየት ከሚችሉ አነስተኛ ከተሞች/ቦታዎች ቤጊ፣ ሜቲ፣ መንዲ፣ ጫልቱ፣ ቡሬ፣ አገው ግምጃ ቤት፣ እንጅባራ፣ ግሽ አባይ፣ ሞጣ፣ ዳሞት፣ ጋይንት፣ ንፋስ መውጫ፣ ጋሸና፣ ሙጃ፣ ዋጃ፣ ቆቦ፣ ኮረም፣ አላማጣ፣ ጊራራ እና ላሊበላ ይገኙበታል፡፡

 በአዲስ አበባ፣ ሐዋሳ፣ ድሬደዋ፣ መቐለ፣ ደሴ፣ አዳማ፣ በመሳሰሉት ከተሞች ቀለበታዊ ግረዶሽ ባይኖርም ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ግን ይኖራቸዋል፡፡

እነዚህን መረጃዎች ሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገፆች ተመልክተናል፡፡ በተለይ መ/ኃ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ በጥልቅ ትንታኔ የሰጡበት ጉዳይ ነው፡፡ ትንታኔውን በደንብ እንድታዳምጡት እፈልጋለሁ፡፡

የጸሃይ ግርዶሽ በዓይን መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን (በተለይም ሬቲና) ላይ ያደርሳል፡፡ የምታመነጨው አልትራ ቫዮሌት ጨረር መታከም የማይችል ጉዳት ያስከትላል፡፡ ሶላር ኢክሊፕስ ቪወር መነፅር በመጠቀም፣ በጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባ የጸሃይ ብርሃን የሚስለውን ቅርፅ በመመልከት ወይም ፒን ሆል ካሜራ በመስራት መመልከት ይቻላል፡፡

ለዚህ ጉዳይ ተብሎ በፋብሪካ በተመረተ ሶላር ኢክሊፕስ መነፅር ካሆነ በስተቀር በማንኛውም መነፅር፣ ካሴት፣ ሲዲ፣ ፊሎፒ ዲስክ፣ በራጅ፣ በመበየጃ መነፀር፣ ጥቁር ድርብርብ መስተዋት ወይም ሌላ ነገር በመጠቀም መመልከት የሚያመጣውን አደጋ መግለፅ እንጂ ሊያልፈን የማይገባውን ክስተት እንዴት ማየት እንዳለብን አማራጭ ነገሮችን ማቅረብ ላይ ሲሰራ አላየሁም፡፡

መነፀሩ በሃገራችን የማይመረት በመሆኑ ማግኘት ስለማይቻልና አቅም እያለን እንኳን አቅርቦት ስለሌለ መጠቀም አንችልም፡፡ እና በዚህ ሁኔታ እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጥ ወይስ አይናችንን መስዋዕት እናድርግ? አሁን ያቀረብኩላችሁ ቀላል መፍትሄ አይናችንንም ሳናጣ፣ ይህ ታሪካዊ የእድሜ ዘመን አጋጣሚ ክስተቱም ሳያመልጠን በቀላሉ በአካባቢ በሚገኙ ቁሳቁስ እንዴት ማዘጋጀት እንደምንችል አሳያችኋለሁ፡፡ የዩቱብ ቻናሉን ሊንክ በመከተል ተመልከቱ፡፡

ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ለምታውቁት ሁሉ አጋሩ፣ ምከሩ፣ ቻናሉንም ውደዱ፣ ቤተሰብ ይሁኑ (ሰብስክራይብ አድርጉ)፣ አስተያየት ካለዎትም ይለግሱን፡፡ ሌላ የምትፈልጉት ጉዳይ ካለም አስተያየት መስጫ ሳጥን ላይ ይላኩልኝ፡፡

በተለይ በገጠር ያሉ ወዳጆቻችሁ በመረጃ እጦት ምክንያት እንዳይደናገጡ፣ እየደወላችሁ ንገሩ፡፡

መኖር መታደል ነው፣ ለመኖር ግን መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ በኮሮና ዘመን ኮሮናን ልናይ ነውና አደራ ራሳችሁንና ወገኖቻችሁን ከኮሮና ጠብቁ! አይናችሁንም ከፀሃይ ግርዶሽ ኮሮና ጠብቁ!

ቸር ይግጠመን!

አዲሱ ቢሆነኝ 10/10/12 ዓ.ም ባህርዳር

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: