የዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ አራተኛ ሥራ “ሰበዝ” መጽሃፍ በገበያ ላይ ዋለ፡፡


የተከበሩ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ በአዲሱ ሰበዝ መፅሃፋቸው ላይ የኔ ፕሮፌሰር በሚለው አንድ ሰበዝ ገፅ 14 ላይ እንዲህ ከተቡት፦

“በልቤ በእውነት ለምን ነበር ወደ ተከበረው ዩኒቨርሲቲ የመጣሁት? ለካ ወደ አውሮፓ ያቀናሁት ለመተቸት፣ ለመታረም ሳይሆን ለመደነቅ ነበር? ለማወቅ ሳይሆን ማወቄን ለማረጋገጥ ኖሯል ። ለካ ወደ አውሮፓ ያቀናሁት ያወቅሁ የመሰለኝን ነገር በሚሰጡኝ ዲግሪ አባብዬ ውስጣዊ ባዶነቴን ተሸክሜ ሰባዶ ጉራ ለመኖር ኖሯል። በዶክትሬት ዲግሪ ተካልዬ በማይምነት ግርሻ ለመሰቃዬት ነበርና አልኩና በእጅጉ በእራሴ አፈርኩ።”  

በጣም ስለገረመኝና የብዙዎቻችንን ህይወት ይቃኝ ስለመሰለኝና አንድታነቡትም መፅሃፉን ለመጋበዝ ያክል ነው ቃል በቃል ያስቀመጥኩት፡፡

እንዲህ እንዲህ እያለ 20 ያክል ርዕሶችን የያዘ በህይወቱ የገጠሙትን አንዳንድ ተሞክሮዎች በመምዘዝ አስተማሪ፣ ገሳጭና አነቃቂ ትምህርቶችን በለዛማ ብዕሩ አስተማረን፣ አነቃቃን፣ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ተስፋ አቆጥቁጦ መኖርን አሳየን፡፡ ጠባብ መንገድና ዕድልን ለማስፋት አጋጣሚና ብስለትን መጠቀም ያስቻሉትን መልካም ተሞክሮዎችን አጋርቶንል፡፡

በመጨረሻ ግን ለዶክተር ዓለማየሁ በርታልን ኑርልን በማለት እናንተ ደግሞ መጽሃፉን ታነቡት ዘንድ ጋበዝኳችሁ…  ሰላም ሁኑልኝ፡፡

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: