ዛሬ በሰቆጣ ከተማ አክራሪነትን በመቃወም ሰልፍ ተወጣ 13/12/2005 ዓ.ም


 

በመላ ሃገሪቱ እንደ ንቅናቄ ተይዞ ባለው የአካራሪነት ተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ ተረኛዋ ሰቆጣ ከተማ ነች፡፡ ከሌሊቱ ጀምሮ ቅስቀሳው ለጉድ ነበር፡፡ ያው ለተቃውሞ ያክል፣ የመንግስት ፍላጎትም ስላለበት እንጂ እኛ ጋ የልማት እንጂ የአክራሪነት ወይም የአሸባሪነት ስሜቱም መንፈሱም የለም፡፡ የሩቅ ወሬ ነው፡፡  ያው በቀበሌ ስለሆነ ቅስቀሳው እያንዳንዱ ይወጣታል፡፡

ምነው ሰቆጣ ሰልፍ በዛባት እንድማትሉ አምናለሁ፡፡ ምክንያቱም፣ ዓላማውም፣ ጉትጎታውም፣ ብሱቱም፣ ህመሙም፣ አንገብጋቢነቱም ይለያያል፡፡

ታስታውሱ እንደሆነ ስለመንገድ መቅረት ሰልፍ ህዝቡ ሲወጣ ያለቀስቃሽ መንገድ ሞልቶ ነበር የጎረፈው፡፡ ኧረ መንገድ ዛሬም ቁስሌ ተነሳብኝ!

በነገራችን ላይ ከጋዝጊብላ ወረዳና ከሰቆጣ ወረዳ የተውጣጡ የግል ባለሃብቶች ለዚህ ለቀረው መንገድ ጥያቄያቸውን በጨዋና ሰላማዊ በሆነ ደንብ ለክልልና ለፌዴራል ለማቅረብ  ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡ እንዲያውም ተራውን ህዝብ ሳይጨምር ነጋዴው ብቻ ከ100000 /መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሰልፈኞችከክልል እስከ ፌዴራል ለሚያደርጉት ሰልፍ መንቀሳቀሻ /ለስራ ማስፈፀሚያ/ አዋጥተዋል የሚል ይፋ ወሬ ሰሞኑን ሰማሁ፡፡

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: