ችግኝ ተከላና የእኛ ሃገር ጋዜጠኛ


ችግኝ ተከላና የእና ሃገር ጋዜጠኛ

ትናንት ለዛሬ ታወጀ “ነገ በጠዋት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ስላለ የቀበሌው ነዋሪዎች የሆናችሁ በመስቀል መተኮሻ እንድተገኙ”

ዛሬ በጠዋት ታወጀ “የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ስላለ የቀበሌው ነዋሪዎች የሆናችሁ በመስቀል መተኮሻ እንድተገኙ” ተባልን፡፡ የቀበሌው ነዋሪ ብቻ ሳይሆን ችግኝ መትከል ግዴታችንም ኃላፊነታችንም ስለሆነ በጠዋት ተገኘን፡፡ እኛ ስንሄድ ስንት ሰው ነበር? የቀበሌው ሊቀመንበር ገበያው ኪሮስና የቀበሌው ለፋፊና ጥሩመባ ነፊ በጣት ከሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ነበሩ፡፡ ተራራው አናት ላይ ወጥተው በዚህ በኩል ኑ… ችግኝ ከዚያ ቤት አለ ይዛችሁ ኑ… እያሉ ይለፍፋሉ፡፡

የቻልነውን ያክል ችግኝ፣ መቆፈሪያ፣ የችግኝ ፕላስቲክ መቅደጃ መቀስ የችግኝ መያዣ እንቅብ/ባርና (ኧረ በሽርጡም የተሸከመ ነበር) የዘን ተራራውን ወጣን፡፡ መትከል ጀመርን፡፡

ጥቂት መምህራን፣ ጥቂት ፖሊሶች ጥቂት የኔ ቢጤ ተራ ተዋሪዎች… ጥቂት  ካሜራዬን አውጥቼ የቻልኩትን አንድ ሁለት አልኩ/አነሳሁ… ለትዝብቱ ብዬ፡፡

በዚህ መሃል ጋዜጠኛዋ ደወለች  ተባለ… ስልኩን ያነሳው ማሞ ሰው ተሰብስቧል ነይ ሲላት ይሰማናል፡፡ ኃላ ስንሰማ ግን ሰው ሙሉ በሙሉ ተሰብስቦ ካሜራ ማን… ጋዜጠኛ ባለበት እንዲሰራ በዚህ መልኩ ለቀረፃ ዝግጁ ሲሆን እንዲደወልላቸው ነበር የሚፈልጉት፡፡

እያለ እያለ…. የሁሉም ቀጠናዎች ነዋሪዎች በጣም ብዙ ፖሊሶች… በጣም ባይባልም ብዙ መምህራንና የመንግስት ሰራተኞች… ብዙ ብዙ ሆንን፡፡ ተከላው ባንድ ጊዜ ለፍሬ ያብቃው! ለከርሞ ለተከላ አይመልሰን! እየተባለ ተጠናቀቀ፡፡ ሁሉም እጁን እያራገፈ… ወደምዝገባ ቦታቸው በምድብ በምድቡ ተገኙ… እኔ የት ብዬ ልመዝገብ… ለራሴ ከነባለቤቴ መዝግቤ ልንመለስ ስንዘጋጅ (እንዲያውም የተመዘገበው ብዙው ሰው እየሄደ ነው) ጋዜጠኛዋ ደወለች ተባለ… ሄሎ አለ ባለ ስልኩ ማሞ… (ልምጣ? አለችው መሰለኝ) እህ! አሁን ምን ታደርጊያለሽ ሰው እኮ ስራ ጨርሶ እየተበተነ ነው ቅድም እኮ ነይ ብዬሽ ነበር… ምነው በጠዋት ተበተኑ? ብሎ ያለችውን አስተጋባና (እኛ እንድንሰማ ይመስለኛል) አይይይ ቁርሱ በቀረብሽ እንጂ… ድምፁ ድክምክም እያለ (ድምፁን እንዳትቀርፀው ፈርቶ ይሁን… እንዳትሰድበው እንጃ) ተበትነዋል ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡

የቁልቁለት መንገዱን ተያይዘን ሳለ በሃሳቤ ትንሽ አውጠነጠንኩ፡፡ አሁን ይህች ጋዜጠኛ ከነሙሉ ቡድኗ ምን እንደምትዘግብ… ከባለቤቴ ጋር ይህን ወግ የእግረ መንገድ አደረግነው… ያው የፈረደበት የቀበሌው ሊቀመንበር ከተተከሉት ችግኞች መሃል ሆኖ ወይም የተተከለ ችግኝ እየነካካ ቃለ-መጠይቅ ይደረግለታል፡፡ የሌላ ቦታ ችግኝ ተካዮች የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች ተብለው ከጀርባ (ባክግራውንድ ይሉታል) ይርመሰመሳሉ… ይንጎዳጎዳሉ፡፡ (ትንሽም ብትሆን… የሬዲዮም ብትሆን የጋዜጠኛን ሥራ እናውቀዋለን) እየተባባልን እውነትም መንገዱ ቀለለን… ቤታችን ደረስን፡፡

Published by Addisu Bihonegn

I'm a beekeeping Researcher in Andassa Livestock Research Center, Amhara , Ethiopia. BSc in Animal Sciences at Haramaya University MSc. in Apiculture at Bahirdar University.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: