Featured

ከፊል ዘመናዊ አናቢነት


ንብ እርባታ ሊባክን የሚችል የተፈጥሮ ሃብትን ወደ ኢኮኖሚ መቀየር የሚያስችል ጥበብና ሳይንስን ማቀናጀት የሚጠይቅ ትልቅ የግብርና ዘርፍ ነው፡፡ በዚህም ማንኛውም ፍጡር ሊያመረርተው ወይም ሊሰራው የማይችላቸውን ነገር ግን በእፅዋት ላይ ያሉ ብናኝና ፈሳሽ ሃብቶችን ወደ ውድና በቀላሉ የማይበላሹ ምርቶች (ማለትም ማር፣ ሰም፣ የንብ ዳቦ፣ የንብ ወተት፣ የንብ ሙጫ፣ የንብ መርዝ) መቀየር ያስችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በብዙዎች ዘንድ አነስተኛ ግምት የሚሰጠው ነገር ግን ከቀጥታ የንብ ውጤት (ምርት) በላይ የሚሰጡት እፅዋትን የማዳቀል ወይም የተራክቦ አገልግሎት ይጠቀሳሉ፡፡ የንብ እርባታ እድሜና ፆታ ሳይለይ በአነስተኛ መነሻ ካፒታል መሰራትና በአጭር ጊዜ ምርት የተሻለ ገቢ ማግኘት ያስችላል፡፡ በተጨማሪም ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የስራ ዘርፍ መሆኑ አንጻራዊ ጠቀሜታውን ከፍ ያደርገዋል፡፡   

ኢትዮጵያ በንብ ቁጥር፣ በማርና ሰም ምርት ከአፍሪካ ቀዳሚ ከሚባሉ ሃገራት ትመደባለች፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ከዘርፉ ምንም የሚጠበቅባትን ያክል እንዳልሰራችና ዘርፉ ለአናቢውም ሆነ ለሃገር ኢኮኖሚ ከ10 በመቶ ያልበለጠ ጥቅም እንዳልሰጠ በዚህም የተነሳ ዘርፉ ያልተነካና ለማዘመንም ሆነ ምርቱን ለማሳደግ ብዙ ሃብት እንደሚገኝ ይታመናል፡፡ ከሃብቶቹ ውስጥ ከ7000 በላይ የሚሆ ለንብ ቀሰምነት የሚውሉ ዕፅዋት ዓይነቶች፣ ከ10 ሚሊዮን የሚልቅ የንብ ቁጥር፣ መሻሻል የሚችል ባህላዊ የአረባብ ዘዴ፣ ልምድ ያላቸው አናቢዎች፣ ከፍተኛ የምርት ፍላጎትና አማራጭ የገበያ መዳረሻዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡  

በንብ እርባታ ውስጥ በአብዛኛው አዕምሮ ላይ የሚመጣውና የሚታወቁት የንብ እርባታ ዘዴዎች በባህላዊ መንገድ በጓሮ ንብ ማርባት፣ በሽግግር ቀፎ እና በዘመናዊ ቀፎ በጓሮ ወይም በተፋሰስ ላይ ንብ ማነብ ናቸው፡፡ በጓሮ በሚያረቡበት ጊዜም ለንብ ጠላቶች መከላከያ፣ ከዝናብና ፀሃይ መከለያ የሚሆን ቤት ወይም የንብ ጋጣ ማዘጋጀት የተለመደ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ባሻገር በብዛት ትላልቅ ዛፎች በሚገኙበት ውስን ቦታዎች በዛፍ ላይ ከ2 እስከ 12 የሚደርሱ የባህላዊ ቀፎዎችን ማንጠልጠል የተለመደ ነው፡፡  

ነገር ግን በአማራ ክልል፣ በአዊ ዞን፣ ጓንጓ ወረዳ፣ ከቻግኒ ከተማ ትንሽ ወጣ ብሎ በተለምዶ ራንች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ ልምድ ያለው አናቢ ተሰርቶ ያየነው የንብ አረባብ ዘዴ ግን የተለየ ነው፡፡  

በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት በአንድ ዛፍ ላይ ለብዙ ህብረ-ንቦች ማስቀመጫ እንዲሁም ከዝናብና ፀሃይ መከለያ የሚሆን በእንጨት በማዘጋጀት አስደማሚ የአንድ ዛፍ የንብ እርባታ ጣቢያ አዘጋጅቷል፡፡ የሚወርደውና የሚወጣው በመሰላል ሲሆን ምንም ዓይነት የንብ ጠላቶች በአካባቢው እንዳይተናኮሉት የዛፉን ግርጌ የተለያዩ የንብ ጠላት መከላከያ ነገሮች (ማለትም አመድ፣ ሽቦ፣ እሾህ የመሳሰሉትን) ያጥረዋል፡፡

በጣም የሚገርመው ነገር በአካባቢው በዛፍ ላይ ቀፎ የመስቀል፣ ማር የመቁረጥና ንቡን የመልቀቅ፤ በድጋሚ ሌላ ቀፎ የመስቀልና ንብ የማጥመድ እንጂ በተደጋጋሚ አንድን ቀፎ ለረዥም ጊዜ መከታተል ልምድ በሌለበት አካባቢ ይህን የአንድ ዛፍ ጣቢያ በማዘጋጀቱ ከፍተኛ የሆነ ምርት በተደጋጋሚ ማምረት ከመቻሉም በላይ ንቦች ቀፏቸውን ለቀው እንደማይሄዱበት ነግሮናል፡፡ ይልቁንም ከሌላ ቀፎ የተሰደዱ ንቦች እየመጡ በወደ አዲስ ቀፎ እንደሚገቡ ከባለቤቱ ለመረዳት ችለናል፡፡  

ስለሆነም በአካባቢው የተንሰራፋውን ንቦችን አጥምዶ የመያዝ አምርቶ የማጥፋት ልምድ የቀለበሰ አሰራር ስለሆነና ከአካባቢው የአረባብ ዘዴ ጋር የተስማማ በመሆኑ በሌሎች አናቢዎችም ቢሰፋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የመጣውን የንብ ቁጥር፣ የምርት ማሽቆልቆል መታደግ ይቻላልና የታየውን ልምድ ማስፋትና ለሞዴል አናቢዎችም ማበረታታት ይገባል፡፡

አዲሱ ቢሆነኝ

የንብ ተመራማሪ

አንዳሳ እንስሳት ምርምር ማዕከል

addbesh@gmail.com

+251911062859

ምስል 1፡- ተለምዷዊ የንብ አሰቃቀል
ምስል 2 ፡- አዲስ የአንድ ዛፍ ጣቢያ
ምስል 3፡- አዲስ የአንድ ዛፍ ጣቢያ
Featured

የንብ እርባታ ምንነትና ጠቀሜታው (ክፍል አንድ)


ሰላም የዚህ ቡድን አባላትና ተከታታዮች እንደምን አላችሁ? እንዴት ከረማችሁ?

ሰላማችሁ ይብዛና ቀደም ሲል በዚህ ቡድን የተለያዩ አዳዲስ መረጃዎችን ከተገኙበት የመረጃ ምንጭ በቀጥታ በማስተላለፍ (ሊንክ ፖስት) ቆይተናል፡፡

ከዚህ በኋላ ከዚህ በፊት በተለመደው ከምናቀርበው በተጨማሪ በተከታታይ ለአናቢዎች፣ ለልማት ጣቢያ ሰራተኞች፣ በአጠቃላይ በንብ እርባታ ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ ሁሉ መረጃ እንዲሰጥ፣ እንዲያስተምርና የሥራ መነሻ መመሪያ የሚሆን ታስቦ በአማርኛ የተዘጋጀ ሰፊ ዝግጅት እናቀርባለን፡፡ ዝግጅቱ የሚያካትታቸው ርዕሰ ጉዳዮችም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡

 • ስለንብ እርባታ ምንነትና ጠቀሜታው
 • ንብ ለማርባት ወይም ለማነብ ምን ምን ሁኔታዎች መሟላት አለበት? እንዴት መጀመር እንችላለን?
 • የንብ እርባታ በኢትዮጵያ ምን ይመስላል ወይም በምን ደረጃ ላይ አለ? ያሉ ተግዳሮቶች ወይም እስካሁን በዘርፉ ለምን አልተጠቀምንም?
 • የንብ ስነ-ፍጥረት ወይም ስነ-ህይወት እና የእያንዳንዳቸው የንብ ቤተሰቦች የሥራ ድርሻ ምን ይመስላል?
 • ህብረ-ንቦችን ማባዛት በምን ሁኔታ፣ መቼና እንዴት ይቻላል?
 • የህብረ-ንብ ዝር ማሻሻል እንዴት ይቻላል?
 • የዘወትርና ወቅታዊ የንብ እርባታ ሥራዎች ምን ምን ናቸው?
 • የንብ ውጤቶች የሚባሉት ምን ምን ናቸው? ጠቀሜታቸው፣ የአመራረት ሂደት፣ የጥራት አጠባበቅ፣ አያያዝ፣ የእሴት ጭማሪና ግብይት ምን መሆን አለበት?  
 • የንብ ጤናን በተመለከተ በተለይም ስለንብ በሽታ፣ ስለንብ ጠላቶች፣ ስለመርዛማ ዕፅዋትና የግብርና ኬሚካል በንቦች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖና መፍትሄዎች ዙሪያ
 • ተፈጥሯዊ የንብ እርባታ መርሆችና ልንከተላቸው የሚገቡ ዓለም አቀፍ ህጎች
 • የመረጃ አያያዝ እና ሌሎችም ወሳኝ የንብ እርባታ ርዕሶችን እያነሳን እንማማራለን፣ እንወያያለን፡፡

በሁሉም ርዕሶች ላይ አለምአቀፍ ተሞክሮዎችንም በማንሳት፣ ጥልቅና ተከታታይ ትንታኔ በመስጠት ለረጅም ጊዜያት አብረን እንቀጥላለን፡፡

ወደፊት በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛዎች (ለምሳሌ በፌስቡክ ቀጥታ ስርጭትና በዩቲዩብ) ለመምጣት ሃሳብ አለን፡፡ ለጊዜው ግን የፌስ ቡክ ግሩፑ (የቡድኑ) https://www.facebook.com/groups/514839721862656 አባል በመሆን ወይም በቴሌግራም ቻናል https://t.me/semonegna በትዊተር ገፅ https://twitter.com/AddisuBihonegn ወይም በቀጥታ ከዌብሳይታችን https://addisubihonegn.wordpress.com/ መከታተል ትችላላችሁ፡፡

ለዛሬ በባዶ እንዳንለያይ ንብ ማርባት ለምን አስፈለገ የሚለውን በአጭሩ እናነሳለን፡፡

የሰው ልጅ ንቦችንና ውጤታቸውን ለራሱ ጥቅም ያዋለበት ጊዜ በውል የሚታወቅ ባይሆንም፡፡

ንቦች በተፈጥሮ ሃብት ላይ ጥገኛ ከመሆናቸው የተነሳ በጫካ፣ በዋሻዎች፣ ለሌሎች እንስሳት ምቹ ባልሆኑ ቦታዎች መኖሪያቸውን በመስራት፣ ጥሩ የቀሰም ዕፅዋት ስብጥር በሚገኝበት አካባቢ ምግባቸውን ከአበባዎች በማዘጋጀት የሚኖሩ ትንንሽ ፍጥረታት ናቸው፡፡ የሰው ልጅም ከዘመናት በፊት ለራሱ እንዲመቸው፣ እንዲቀርበውና እንዲጠቀምባቸው ሲል ንቦችን መቆጣጠርና ማርባት ጀመረ፡፡ ስለሆነም ንብ እርባታ ማለት የንብ ውጤቶችን ለሰው ልጅ ጥቅም እንዲውል የማድረግ ጥበብና ሳይንስ ነው፡፡

ንብ ማነብ ለምን ይጠቅማል?

አንድን ሥራ ከመጀመራችን ወይም ወደዘርፉ ከመግባታችን በፊት ስለጠቀሜታዎቹ በተለይም አንፃራዊ ጠቀሜታው ከሌሎች የተሻለና አዋጭ መሆኑን መረዳት ይጠበቅብናል፡፡ በንብ እርባታም ለመሰማራት ካሰብን እንዲሁ ማወቅ ያለብንን ሁሉ በውል ተረድተን መሆን ይገባዋል፡፡

ንብ ማነብ ለምን ይጠቅማል ብንባል ብዙዎቻችን ለማር ምርት፣ ከማር በሚገኝ ገንዘብ ለመጠቀም ከሚሉ ጥቂት ጠቀሜታዎች ውጪ ብዙም ስንጠቅስ አንታይም፡፡ ምክንያቱም በታዳጊ ሃገራት የንብ እርባታ ከማር ማምረት የዘለለ ጠቀሜታ ሲሰጥ አልታየም፡፡ በተወሰነ መልክ ሰም እንደሁለተኛ ምርት ተደርጎም ቢሆን (ማሩ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ እንደተረፈ ምርት ማለት ነው) እፎ አልፎ ጥቅም ሲሰጥ ይታያል፡፡ ነገር ግን የንብ ጠቀሜታ ከዚህ ላቅ ያለ የሰው ልጅ ህልውና መሰረት የሆኑ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ እነዚንም ጠቀሜታዎች በሦስት ዘርፎች ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ አንደኛው ዘርፍ ላይ ያየነው ጠቀሜታ ሌላው ላይ ሊደገም ይችላል፡፡ ነገር ግን ዘርፎችን ለማጠናከር እንዲቻል ነው፡፡

 1. እንደማንኛውም የግብርና ዘርፍ አጠቃላይ ጠቀሜታው
 2. ልዩ ልዩ ጠቀሜታዎች (ቤተሰባዊ፣ ለሃገራዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ ማኅበራዊ ፋይዳ)
 3. አንፃራዊ ጠቀሜታዎች (ከሌሎች የስራ ዘርፎች በተለይም ሰብል ማምረት፣ እንስሳት እርባታ ከመሳሰሉ የግብርና ዘርፎች አንፃር ያለው  ተቀሜታ)

በሚቀጥለው እያንዳንዳቸውን ጠቀሜታዎች በዝርዝር ይዤ እመለሳለሁ፡፡

ላይክ፣ ሼር፣ በማድረግ እንዲሁም ተጠቃሚ መሆን አለባቸው የምትሏቸውን እዲቀላቀሉ በመጠቆም (suggest በማድረግ) የተጠቃሚውን አባል ቁጥር እንድታሳድጉ እንዲሁም ወደፊት ምን መስተካከልና መካተት እንዳለባቸው አስተያየት በመስጠት እንድትተባበሩን ትጠየቃላችሁ፡፡

መልካም ጊዜ!

በሰላም እንገናኛለን!!

ባህላዊ የሚመስሉን የምግብ አዘገጃጀቶቻችን በሳይንሳዊ መንገድ ሲቃኙ


ባህላዊ የሚመስሉን የምግብ አዘገጃጀቶቻችን በሳይንሳዊ መንገድ ሲቃኙ

አዲሱ ቢሆነኝ ሐምሌ 26/2013 ዓ.ም

ማብቀልና ማቡካት በሰብል በተለይም በሩዝ፣ በማሽላ እና በእንቁ ዳጉሳ ላይ የተመሠረተ፣ ለሰውና እንስሳት እድገት አስፈላጊ ተጨማሪ የምግብ ማዕድናት ተገኝነት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ኬሚካላዊ ይዘት፣ አጠቃላይ ጣዕም፣ ተበይነትና ተፈላጊነት ላይም ከፍተኛ ውጤት አምጥቷል፡፡

የምርምር ውጤቶቹን ለማየት ከዚህ በታች ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ

 1. https://www.researchgate.net/publication/26563652_Effect_of_Germination_and_Fermentation_of_Pearl_Millet_on_Proximate_Chemical_and_Sensory_Properties_of_Instant_Fura-_A_Nigerian_Cereal_Food
 2. https://agris.fao.org/agris-search/search.do?recordID=KR2008000574
 3. https://www.researchgate.net/publication/26563746_The_Effects_of_Germination_of_Low_-_Tannin_Sorghum_Grains_on_its_Nutrient_Contents_and_Broiler_Chicks_Performance
 4. https://pubmed.ncbi.nlm.nih.gov/15796598/
 መልካም ጊዜ! 
በዘርፉ አዳዲስ ወቅታዊ አስተማሪ መረጃዎች እንዲደርስዎ ከዚህ በታች ያሉትን ሚዲያዎች ይቀላቀሉ ወይም አባል ይሁኑ፡፡ 

ዌብሳይት፡ https://wordpress.com/view/addisubihonegn.wordpress.com

ቴሌግራም፡ https://t.me/semonegna

ፌስቡክ ግሩፕ፡ https://www.facebook.com/groups/514839721862656 
ትዊተር፡ https://twitter.com/AddisuBihonegn 
ከወደዱት Like, Comment, Follow እና Share ማድረግዎን እንዳይረሱ፡፡  

የተለያዩ የማር ዓይነቶችን እና መጠንን በመጠቀም የቤታ ዓሳ (Betta splendens) እጭ ተባዕታይነት ምጣኔ ጭማሪ ማሳየቱን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡


የተለያዩ የማር ዓይነቶችን እና መጠንን በመጠቀም የቤታ ዓሳ (Betta splendens) እጭ ተባዕታይነት ምጣኔ ጭማሪ ማሳየቱን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
               ትርጉም፡- አዲሱ ቢሆነኝ ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም
Betta splendens

ወንድ ቤታ ዓሳ በጣም ቆንጆ የሰውነት ቅርፅ እና ቀለም ስላላቸው ከሴት ቤታ ዓሳ የበለጠ ተወዳጅ እና ውድ ናቸው። የወንድ ዓሳውን ቁጥር ለመጨመር አንድ ጥረት የዓሳውን ጾታ ወደ ተባዕት ለመቀየር የሚደረግ ዘዴ ነው፣ ስለሆነም ትርፉ ከፍ ያለ ነው። በአጠቃላይ፣ የፆታ መቀልበስ የስቴሮይድ ሆርሞን ይጠቀማል መጥለቅ ፣ መርፌ ወይም በምግብ በኩል በአፍ በሚለው ዘዴ 17α- methyltestosterone (MT) ይጠቀማል።  ሆኖም፣ ይህ የMT ሆርሞን ብክለትን፣ በተጠኚ እንስሳት ላይ የጉበት ጉዳትን ሊያስከትል እና ሞት ሊያስከትል የሚችል የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉት። ይህ ጥናት የተከናወነው በተለያዩ ማር ዓይነቶች በማጥለቅ እጮቹን በሕይወት የመቆየት እና የወንድ ቤታ ዓሳ መቶኛ የመጨመር ሁኔታ ለማወቅ ነው።

በዚህ ጥናትም የተፈጥሮ ማር የተሻለ ውጤት (97%) ተገኝቶበታል፡፡ 
http://scholar.google.com/scholar_url?url=http://jperairan.unram.ac.id/index.php/JP/article/download/238/138&hl=en&sa=X&d=9304910038386354439&ei=tWgEYcbRF4qImgHdz7SYBQ&scisig=AAGBfm0CJfUl7_iDhy-9oJuuo_W6q7P9nw&nossl=1&oi=scholaralrt&hist=TiyO4cYAAAAJ:6060489960267510365:AAGBfm1tfPROZXluHcBAqMpL9GoKea1IyQ&html=&folt=kw 
በተጨማሪም በተመሳሳይ ጥናት የተፈጥሮ ማር መጠንን (concentration) በማለያየት ማለትም 5፣ 6 እና 7ሚሊ/ሊ በማጥለቅ እጮቹን በሕይወት የመቆየት እና የወንድ ቤታ ዓሳ መቶኛ የመጨመር ሁኔታ ለማወቅ ተችሏል። በዚህ ጥናትም በ7ሚሊ/ሊ የተፈጥሮ ማር ማጥለቅ የተሻለ ውጤት (100%) ተገኝቶበታል፡፡ 
https://ui.adsabs.harvard.edu/abs/2020E%26ES..584a2050S/abstract 
ሙሉ ፅሁፉን ማበብ ለሚፈልግ ከላይ ያሉትን ሊንኮች መጠቀም ይቻላል፡፡ 
 
መልካም ጊዜ! 
 
በዘርፉ አዳዲስ ወቅታዊ አስተማሪ መረጃዎች እንዲደርስዎ ከዚህ በታች ያሉትን ሚዲያዎች ይቀላቀሉ ወይም አባል ይሁኑ፡፡ 

ዌብሳይት፡ https://wordpress.com/view/addisubihonegn.wordpress.com

ቴሌግራም፡ https://t.me/semonegna

ፌስቡክ ግሩፕ፡ https://www.facebook.com/groups/514839721862656 
ትዊተር፡ https://twitter.com/AddisuBihonegn 
ከወደዱት Like, Comment, Follow እና Share ማድረግዎን እንዳይረሱ፡፡  


የአመጋገብ ጉዳት እና አዲስ ሲስተሚክ ፀረ-ተባይ (flupyradifurone, Sivanto ®) የንብ መዳንን፣ የምግብ ፍጆታን፣ የበረራ ስኬታማነትን እና የቀፎ ሙቀት መቆጣጠርን ይቀንሳል፡፡ 


የአመጋገብ ጉዳት እና አዲስ ሲስተሚክ ፀረተባይ (flupyradifurone, Sivanto ®) የንብ መዳንን፣ የምግብ ፍጆታን፣ የበረራ ስኬታማነትን እና የቀፎ ሙቀት መቆጣጠርን ይቀንሳል፡፡ 

ሥር የሰደደ የአመጋገብ ጉዳት እና አዲስ ሲስተሚክ ፀረ-ተባይ በተናጠል ወይም በጥምር የንብ ጤናን በመጉዳት የመሞት እና የመጥፋት አደጋ ሊያስከት ይችላሉ፡፡   

https://www.academia.edu/39932703/Combined_nutritional_stress_and_a_new_systemic_pesticide_flupyradifurone_Sivanto_reduce_bee_survival_food_consumption_flight_success_and_thermoregulation?email_work_card=view-paper

በአግሮ-ሥነ-ምህዳር ውስጥ የአግሮ ኬሚካሎች አጠቃቀም እና የአዳቃይ ነፍሳት ማሽቆልቆል ትስስር።


በአግሮ-ሥነ-ምህዳር ውስጥ የአግሮ ኬሚካሎች አጠቃቀም እና የአዳቃይ ነፍሳት ማሽቆልቆል ትስስር።

Emily N. Kitivo, Prof. Gedion H. Nyamasyo, Dr. Jacinta M. Kimiti, Prof. Josphert N. Kimatu

ትርጉም፡- አዲሱ ቢሆነኝ ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም

ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በሚሄድ ሕዝብ ብዛት ምክንያት ዓለም የመገቡ አፍ የሚበዛባት ቦታ እየሆነች ነው፡፡ ይህም በአካባቢያችን እነዚህን ተመጋቢ አፎች የመደገፍ አቅም ላይ  ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ ነው፡፡ የአፍሪካ አገራት ግብርናን በዘመናዊ መንገድ በማዘመን ለፈተናዎች ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡ አብዛኛው የዚህ ከፍተኛ እርሻ በአግሮኬሚካሎች አተገባበር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ሆኖም የኬሚካል ማዳበሪያና ፀረ-ተባዮች አጠቃቀም ሌሎች ቀደም ሲል ያልታሰቡ ተግዳሮቶች ይዘው መጥተዋል፡፡ 
ይህ ጥናት የተካሄደው የአግሮኬሚካሎች አጠቃቀም እና በአግሮ-ስነ-ምህዳሮች ውስጥ በአዳቃይ ነፍሳት ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ለመገምገም ነው፡፡ ምርምሩ የተካሄደው በኬንያ በማቻኮስ ካውንቲ ውስጥ በሙአ ሂልስ አካባቢ ነው፡፡ በመጠይቆች አማካኝነት የተለዩ ናሙናዎችን በመጠቀም በእርሻ ላይ በሚገኙ አግሮኬሚካሎች ላይ መረጃ ተሰብስቧል፡፡ በመስክ ቅኝቶች ወቅት በእርሻዎቹ ውስጥ የሚገኙ የነፍሳት  ብዝሃነት እና ብዛት ናሙናዎችን ለማመልከት የፓን ወጥመዶች (Pan traps ) ያገለግሉ ነበር፡፡ ጥናቱ እንዳመለከተው 80% የሚሆኑት አርሶ አደሮች ፀረ-ተባዮች እና ፀረ-ፈንገስ መድኃኒቶችን ሲጠቀሙ 20% የሚሆኑት ደግሞ ቅጠላ ቅጠል ማዳበሪያን ይጠቀማሉ፡፡ የስፒርማን ትስስር ትንተና እንደሚያመለክተው በተጠቀመው የአግሮኬሚካሎች ዓይነት እና በነፍሳት ብዛት መካከል ከፍተኛ ግንኙነት አለ (r2 = 0.402, p<0.028)። ይህ ጥናት በአሁኑ ወቅት የኬሚካል ማዳበሪያዎች እና ፀረ-ተባዮች አጠቃቀም የሥነ-ምህዳር ስርዓት መበላሸትን እንደሚያመጣ እና የአዳቃይ ነፍሳት ቁጥርና ብዝሃነትን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ቁጥጥር ሊደረግበት እንደሚገባ ደምድሟል፡፡ ስለሆነም ሥነ ምህዳራዊ አገልግሎት ሰጭዎችን እና ተግባሮቻቸውን ለመደገፍ ሲባል በአስቸኳይ የአግሮ-ምህዳሮች አካባቢያዊ አያያዝ ስርዓት መዘርጋት እንዳለበት ግኝቶቹ ያስተጋባሉ፡፡
 
ሙሉ ፅሁፉን ማበብ ለሚፈልግ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ መጠቀም ይቻላል፡፡ 
https://jriiejournal.com/wp-content/uploads/2021/06/JRIIE-5-2-008.pdf
መልካም ጊዜ! 
 
በዘርፉ አዳዲስ ወቅታዊ አስተማሪ መረጃዎች እንዲደርስዎ ከዚህ በታች ያሉትን ሚዲያዎች ይቀላቀሉ ወይም አባል ይሁኑ፡፡ 

ዌብሳይት፡ https://wordpress.com/view/addisubihonegn.wordpress.com

ቴሌግራም፡ https://t.me/semonegna

ፌስቡክ ግሩፕ፡ https://www.facebook.com/groups/514839721862656 
ትዊተር፡ https://twitter.com/AddisuBihonegn 
ከወደዱት Like, Comment, Follow እና Share ማድረግዎን እንዳይረሱ፡፡  

የመመገቢያ ዓይነት በህብረ-ንብ እና የአመጋገብ ወቅት የቀፎ ክወና ላይ ያለውን ተጽዕኖ ያሳየ ጥናት በሆለታ ንብ ምርምር ማዕከል ይፋ ሆኗል፡፡


Zewdu Ararso Hora, Taye Negera, Kibebew Wakjira

ትርጉም፡- አዲሱ ቢሆነኝ ሐምሌ 14/2013 ዓ.ም

በርካታ የንብ መንጋ መመገቢያ ዓይነቶች በንብ አናቢዎች ንቦቻቸውን በስኳር ሽሮፕ ለመመገብ ያገለግላሉ፡፡ ሆኖም፣ እያንዳንዱ የመመገቢያ አይነት ለንቦችም ሆነ ለንብ አናቢዎች ጥቅሞች እና ድክመቶች አሉት፡፡ የተለያዩ መመገቢያ ዓይነቶች በህብረ-ንቦች ደህንነት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ እና በንብ አናቢዎች ለመመገብ የሚያስችላቸው ምቹ ሁኔታ ታይቷል፡፡ የንብ መንጋን ለመመገብ የሚያስፈልግ ጊዜ፣ የሚጠቀመው ምግብ መጠን፣ በምግብ ወቅት የሞቱ ንቦች ብዛት፣ ሲወገዱ በመመገቢያው ውስጥ/ላይ የሞቱ ንቦች ብዛት፣ በቴክኒሻኖች አስተያየት ላይ የተመሠረተ የመረበሽና እና ምቾት ንፅፅር ተደርጓል፡፡ በዚህ መሠረት ከባልዲ (71.25 ሰከንድ) እና ፍሬም (137.80 ሰከንድ) መመገቢያዎች ይልቅ በላይ በኩል መመገቢያ በጣም አጭር ጊዜ (40.45 ሴኮንድ) ወስዷል፡፡ እንደዚሁም በቅደም ተከተል 5.45 እና 11.00 ከቀፎ ስር የሞቱ ንቦች ከተመዘገቡበት ባልዲ እና የፍሬም መመገቢያ ጋር ሲነፃፀር በላይ በኩል ህብረ-ንብን በሚመግብበት ጊዜ አነስተኛ (p <0.001) የሞቱ ንቦች ቁጥር (2.50) ታይተዋል፡፡ በተጨማሪም 1.60 የሞቱ ንቦች ከተቆጠሩበት የፍሬም መመገቢያ ጋር ሲነፃፀር ከላይኛው መመገቢያ የላይኛው ገጽ ላይ ምንም የሞተ ንብ አልተመዘገበም፡፡ ሆኖም የመመገቢያ ዓይነት በሙከራው ወቅት የተበላውን የስኳር መጠን እና የህብረ-ንብ አቅም ላይ ተጽዕኖ አልፈጠረም፡፡ የንብ ቴክኒሻኖችን አስተያየት በተመለከተ የላይኛው መመገቢያ ህብረ-ንብን በአነስተኛ ረብሻ እና ጉዳት ለመመገብ በጣም ምቹ ነው፡፡ ስለሆነም የወቅቱ ውጤቶች እንደሚያመለክቱት የላይኛው መመገቢያን በመጠቀም ንቦችን መመገብ አነስተኛ ጊዜ የሚወስድ፣ ለንብ አናሳ ጉዳት የሚያደርስ እና ለንብ አናቢው የተሻለ የመመገቢያ ዘዴን ነው፡፡

 
ሙሉ ፅሁፉን ማበብ ለሚፈልግ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ መጠቀም ይቻላል፡፡ 
http://ajbioeng.org/article/217/10.11648.j.bio.20210903.15 
መልካም ጊዜ! 
 
በዘርፉ አዳዲስ ወቅታዊ አስተማሪ መረጃዎች እንዲደርስዎ ከዚህ በታች ያሉትን ሚዲያዎች ይቀላቀሉ ወይም አባል ይሁኑ፡፡ 

ዌብሳይት፡ https://wordpress.com/view/addisubihonegn.wordpress.com

ቴሌግራም፡ https://t.me/semonegna

ፌስቡክ ግሩፕ፡ https://www.facebook.com/groups/514839721862656 
ትዊተር፡ https://twitter.com/AddisuBihonegn 
ከወደዱት Like, Comment እና Share ማድረግዎን እንዳይረሱ፡፡  

ለሰብል ጥበቃ የምንጠቀማቸው ፀረ ተባይ መድኃኒቶች በንቦች ላይ ተፅዕኖ ያለው መሆኑ አንድ የግምገማ ጥናት ያሳያል፡፡


ለሰብል ጥበቃ የምንጠቀማቸው ፀረ ተባይ መድኃኒቶች በንቦች ላይ ተፅዕኖ ያለው መሆኑ አንድ የግምገማ ጥናት ያሳያል፡፡

Sapna Devi, Diksha Devi and Sawraj Jit Singh

ትርጉም፡- አዲሱ ቢሆነኝ ሐምሌ 09/2013 ዓ.ም

የማር ንቦች በአበባ ዘርን በማዳቀል የሚረዱ፣ የፍራፍሬ ምርትን ከፍ የሚያደርጉ እንዲሁም በብዙ የፍራፍሬ ሰብሎች ውስጥ የፍራፍሬ መውደቅን የሚቀንሱ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ሀብቶች-ነፍሳት ናቸው፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በንብ ቁጥር ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሽቆልቆል ታይቷል፡፡ ንቦች አበባን በሚቀስሙበት ጊዜ እንደ ፀረ-ተባዮች ያሉ ለተለያዩ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ኬሚካላዊ ንጥረ ነገሮች የተጋለጡ ናቸው፡፡ 
ከተረጩት ፀረ-ተባዮች ከ98% በላይ የሚሆኑት መዳረሻቸው ዒላማ ያልሆኑ ዝርያዎችን፣ አየርን፣ ውሃን እና አፈርን ጨምሮ ከታለሙባቸው ዝርያዎች ውጭ ወደ ሌላ ይደርሳሉ፡፡ ከሌሎች ነፍሳት ጋር ሲነፃፀር ንቦች የፀረ-ተባይ ማጥፊያ ኢንዛይሞችን በሚቀይሩ ጂኖች እጥረት የተነሳ ለፀረ-ተባይ መድሃኒቶች በጣም የተጋለጡ ናቸው፡፡ 
አብዛኛዎቹ ፀረ-ተባዮች የሚረጩት በትነት፣ በፈሳሽ እና በብናኝ መልክ ነው፡፡ የሚረጨው ኬሚካል በቀጥታ በሚታከሙ ማሳዎች ላይ ባሉና በሚበሩ ንቦች ላይ ሊወድቅ ይችላሉ፡፡ የንቦች በአደገኛ ፀረ-ተባይ መርዝ መመረዝ ሲኖር የሚያሳዩት ዓይነተኛ ክሊኒካዊ ምልክቶች መጨናነቅ፣ የተዛባ ባህሪ እና ያልተለመዱ የክንፍ እንቅስቃሴን ያካትታሉ፡፡ በኒዮኒኮቲኖይዶች (neonicotinoids) መርዝ ከተጠቁ በኋላ እንዲህ ዓይነቱ የሠራተኛ ንቦች መጥፎ ባሕርይ ምልክቶች በተጎዱት ቀፎዎች ውስጥ በ71.4% ውስጥ ታይቷል፡፡ በአሁን ግምገማ በንቦች ከፀረ-ተባይ መርዝ ጋር ስለሚዛመዱ ሁሉም ጉዳዮች ተገምግሟል፡፡ 
 ሙሉ ፅሁፉን ማበብ ለሚፈልግ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ መጠቀም ይቻላል፡፡ 
 መልካም ጊዜ! 
በዘርፉ አዳዲስ ወቅታዊ አስተማሪ መረጃዎች እንዲደርስዎ ከዚህ በታች ያሉትን ሚዲያዎች ይቀላቀሉ ወይም አባል ይሁኑ፡፡ 

ዌብሳይት፡ https://wordpress.com/view/addisubihonegn.wordpress.com

ቴሌግራም፡ https://t.me/semonegna

ፌስቡክ ግሩፕ፡ https://www.facebook.com/groups/514839721862656 
ትዊተር፡ https://twitter.com/AddisuBihonegn 
ከወደዱት Like, Comment እና Share ማድረግዎን እንዳይረሱ፡፡  

ተፈጥሮን ወደነበረበት መመለስ ካልተቻለ የ2 ትሪሊዮን ፓውንድ የኢኮኖሚ ውድቀት ሊገጥመው እንደሚችል የዓለም ባንክ አስጠነቀቀ፡፡


ተፈጥሮን ወደነበረበት መመለስ ካልተቻለ የ2 ትሪሊዮን ፓውንድ የኢኮኖሚ ውድቀት ሊገጥመው እንደሚችል የዓለም ባንክ አስጠነቀቀ፡፡
ሰኔ 29/2013 ዓ.ም
 
ሥነ ምህዳራዊ ጉዳቶች ከፍተኛ ደረጃ ከደረሱ እና አገራት ተፈጥሮን ለመጠበቅ እና ወደነበረበት ለመመለስ የበለጠ ኢንቬስት ማድረግ ካልቻሉ የዓለም ኢኮኖሚ በ 2030 ወደ 2 ትሪሊዮን ፓውንድ የሚጠጋ ዓመታዊ ኪሳራ ይገጥመዋል ሲል የአለም ባንክ አረንጓዴ መር-ኮቪ-19 መልሶ ለማቋቋም ጥሪ ባቀረበበት ወቅት አሳውቋል፡፡ 
ባንኩ በመጀመሪያው ‘የኢኮኖሚ ጉዳይ ለተፈጥሮ’ ሪፖርቱ ውስጥ ምን ያህል ኢኮኖሚዎች በብዝሃ ሕይወት ላይ እንደሚተማመኑ እና በተፈጥሮ የሚሰጡ የተወሰኑ አገልግሎቶች ቢወድሙ እንዴት እንደሚቋቋሙ ተመልክቷል፡፡ ባንኩ ከሰሃራ በታች ያሉ አፍሪካ እና ደቡብ እስያ ሃገራት ላይ የሚደርሰው ጉዳት በጣም የከፋ እንደሚሆን አሳውቋል፡፡
ፀሃፊ Michael Taylor
ምንጭ፡- https://www.scotsman.com/news/environment/restore-nature-or-face-ps2-trillion-economic-blow-warns-world-bank-3294598
 
መልካም ጊዜ! 
በዘርፉ አዳዲስ ወቅታዊ አስተማሪ መረጃዎች እንዲደርስዎ ከዚህ በታች ያሉትን ሚዲያዎች ይቀላቀሉ ወይም አባል ይሁኑ፡፡ 

ዌብሳይት፡ https://wordpress.com/view/addisubihonegn.wordpress.com

ቴሌግራም፡ https://t.me/semonegna

ፌስቡክ ግሩፕ፡ https://www.facebook.com/groups/514839721862656 
ከወደዱት Like, Comment እና Share ማድረግዎን እንዳይረሱ፡፡ 
 

የሰብል አርሶ አደሮች ንቦችን ማርባት አለባቸው፡፡ ለምን ካሉ እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች ማወቅ አለብን፡፡


Bees pollinating flowers የሰብል አርሶ አደሮች ንቦችን ማርባት አለባቸው፡፡ ለምን ካሉ እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች ማወቅ አለብን፡፡ አዲሱ ቢሆነኝ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም የአበባ ዘር አዳቃይ ነፍሳት ከምንመገበው ምግብ በተጨማሪ አየርን የሚያፀዱ፣ አፈርን የሚያረጋጉ፣ ከከባድ የአየር ሁኔታ የሚከላከሉ እና ሌሎች የዱር እንስሳትን የሚደግፉ ጤናማ ሥነ ምህዳሮች እንዲኖሩ ያግዛሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ በአበባ አዳቃይ ነፍሳት […]

የሰብል አርሶ አደሮች ንቦችን ማርባት አለባቸው፡፡ ለምን ካሉ እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች ማወቅ አለብን፡፡

የሰብል አርሶ አደሮች ንቦችን ማርባት አለባቸው፡፡ ለምን ካሉ እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች ማወቅ አለብን፡፡


Bees pollinating flowers
የሰብል አርሶ አደሮች ንቦችን ማርባት አለባቸው፡፡ ለምን ካሉ እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች ማወቅ አለብን፡፡

አዲሱ ቢሆነኝ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም

የአበባ ዘር አዳቃይ ነፍሳት ከምንመገበው ምግብ በተጨማሪ አየርን የሚያፀዱ፣ አፈርን የሚያረጋጉ፣ ከከባድ የአየር ሁኔታ የሚከላከሉ እና ሌሎች የዱር እንስሳትን የሚደግፉ ጤናማ ሥነ ምህዳሮች እንዲኖሩ ያግዛሉ፡፡

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ በአበባ አዳቃይ ነፍሳት በተለይም በንቦች ላይ ጥገኛ የሆነው የግብርና ምርት መጠን ወደ 300 በመቶ ገደማ አድጓል፡፡

በዓለም ዙሪያ ካሉ አራት ሰብሎች መካከል ሦስቱ ለሰው ልጅ ለምግብነት አገልግሎት የሚውሉ ፍራፍሬዎችን ወይም ዘሮችን የሚያመርቱ ሲሆን ቢያንስ በከፊል በንቦች ላይ ጥገኛ ናቸው፡፡ የአበባ ዘር አዳቃይ ነፍሳትን (በተለይም ንቦችን) ብዛት እና ብዝሃነትን ማሻሻል የሰብል ምርትን ያሳድጋል፡፡ የአበባ ዘር አዳቃይ ነፍሳት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙት የምግብ ሰብሎች 35 ከመቶው የምግብ ሰብሎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡ 
እኛ የምንበላቸውን በብዙ ጥቃቅን ንጥረ-ምግቦች የበለፀጉ ፍራፍሬዎችን፣ አትክልቶችን፣ የቅባት እህሎች፣ እና ሌሎች ዘሮችን ለማምረት የአበባ ዘር አዳቃዮች በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነገር ግን በሰብል አበባ ማዳቀል አገልግሎቶች ላይ ቀስ በቀስ ያለማቋረጥ ማሽቆልቆል እየታየ ነው። ቀደም ባሉት ጊዜያት ይህ አገልግሎት በተፈጥሮ ያለምንም ክፍያ ይቀርብ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን የእርሻ ማሳዎች ሰፋፊ ሆነዋል፣ የግብርና ልምዶችም እንዲሁ በውስን ሰብሎች እና በኬሚካሎች አጠቃቀም ላይ በማተኮር ተለውጧል፡፡ 
በእርግጥ ለሰው ልጅ ፍጆታ ፍራፍሬዎችን እና ዘሮችን ከሚያመርቱ የአለም ሰብሎች ወደ 75 ከመቶው የሚጠጋው ቢያንስ በከፊል ለምርት ቀጣይነት፣ ምርት ብዛት እና ጥራት ሲባል በአበባ ዘር አዳቃይ ንቦች ላይ ጥገኛ ነው፡፡ የሚቀርበው ብዝሃ-ምግብ በአብዛኛው የእነዚህ አዳቃዮች ዕዳ ነው፡፡ 
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ለአበባ ዘር አዳቃዮች፣ በተለይም ለንቦች በከፍተኛ የከፋ ማሽቆልቆል መንስኤ ናቸው፡፡ ማሽቆልቆሉ ቀድሞውኑ በሰብል ምርት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ እና በቫይታሚን የበለፀጉ ሰብሎች እንደ ፍራፍሬና አትክልት ወጭዎች ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ያልተመጣጠኑ አመጋገቦች እንዲሁም እንደ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያሉ የጤና እክሎችን ያስከትላል፡፡ 
 የ2018 የምግብ እና እርሻ ድርጅት ሪፖርት ‘ንቦች እና ሌሎች የአበባ ዘር አዳቃዮች ለምግብ እና ለግብርና አስፈላጊነት’ በሚል ርዕስ የአበባ ዘር ማዳቀልን (pollination) በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ምርት ለማግኘት ጉልህ የግብርና አስተዋፅዖ አበርክቷል፡፡ ስለሆነም ንቦች እና ሌሎች የአበባ ዘር አዳቃዮች ለግብርና አስፈላጊ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡ 
 እንደ አለመታደል ሆኖ በአብዛኛው የዓለም ክፍሎች ውስጥ የአበባ ዘር ማዳቀል አገልግሎቶች እየቀነሱ ያሉ አዝማሚያዎችን እያሳዩ ነው፡፡ ለምሳሌ በግብርና ልማት ስር በአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎች ውስጥ ምርትን ማቆየት እና መጨመር ለጤና፣ ለምግብ፣ ለምግብ ዋስትና እና ለአነስተኛ አርሶ አደሮች የተሻለ ገቢ አስፈላጊ ነው፡፡ 
 ንቦች የሚሰጡን ጥቅሞች ከሰው ምግብ በላይ ናቸው፡፡ የዱር አዳቃይ ነፍሳትን በሚደግፉ ልምዶች የአበባ ዘር ማዳቀል አገልግሎቶችን እንዲሰጥ በተፈጥሮ ላይ ሆን ተብሎ ሊሰራበት ይገባል፡፡ ያ አሠራር እንደ ማንኛውም እንስሳ ሁሉ ንቦችን ማቆየት ብቻ ነው፡፡ 
 በዓለም ላይ በንብ ውጤቶች ከሚገኘው ገቢ ይልለቅ ንቦች ለእፅዋት የሚያደርጉት የማዳቀል አስተዋፅኦ ግምታዊ ዋጋ ላቅ ያለ መሆኑ አሁናዊ የምርምር ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለሆነም በእነዚህ ሁኔታዎች ሲቃኝ ንብን ማርባት ያለባቸው የሰብል አምራች አርሶ አደሮች መሆን ይገባቸዋል፡፡ ወይም ደግሞ የንብ እርባታውን ዘርፍ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 መልካም ጊዜ! 
 በዘርፉ አዳዲስ ወቅታዊ አስተማሪ መረጃዎች እንዲደርስዎ ከዚህ በታች ያሉትን ሚዲያዎች ይቀላቀሉ ወይም አባል ይሁኑ፡፡ 

ዌብሳይት፡ https://wordpress.com/view/addisubihonegn.wordpress.com

ቴሌግራም፡ https://t.me/semonegna

ፌስቡክ ግሩፕ፡ https://www.facebook.com/groups/514839721862656 
ከወደዱት Like, Comment እና Share ማድረግዎን እንዳይረሱ፡፡ 

ለመሆኑ ያለ ንቦች መኖር እንችላለን?


አዲሱ ቢሆነኝ ግንቦት 27/2013 ዓ.ም ባህርዳር

የማር ንቦች ለግብርና ምርትና ምርታማነት ማደግ እንዲሁም ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ 
ብዙውን ጊዜ ስለንቦች መጎዳት ተከራካሪዎች አናቢዎች ብቻ ናቸው፡፡ መሆን የነበረበት ግን በተገላቢጦሽ የእፅዋት ልማት ሰዎች ወይም ተንከባካቢዎች ይበልጡንም ሁሉም ወገኖች ነበር፡፡

ለመሆኑ ያለ ንቦች መኖር እንችላለን?

በአጭሩ፣ ያለ ንቦች መኖር አንችልም፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ግብርና መምሪያ እንደ ንብ እና ቢራቢሮ ያሉ የአበባ አዳቃይ ነፍሳት በዓለም ላይ ከሚበቅሉት የአበባ እጽዋት ውስጥ 75 በመቶውን በማዳቀል የተክሉን ዘር በማስቀጠል፣ የምርት ብዛት እና ጥራት ጭማሪ ላይ ያግዟቸዋል ብሏል፡፡ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ጨምሮ ከዓለም የምግብ ሰብሎች ውስጥ 35 ከመቶውን ያዳቅላሉ፡፡

ንቦች በአንድ ቀን ውስጥ እስከ 5,000 አበባዎችን መጎብኘት ይችላሉ፡፡ ንቦች ለሰው ልጅ ህይወት ማለት ናቸው… ዓለም በንቦች እጅ ናት… ንቦች ደግሞ በሰዎች እጅ ናቸው፡፡ ለራሳችን ስንል እንንቃ… ንቦቻችንን እንጠብቅ…

የዓለም የምግብ አቅርቦትን ከማረጋገጥ እና ለእሱ ቀጥተኛ ተጠያቂ የሆኑትን አዳቃይ ንቦችን ከመጠበቅ የበለጠ ጥሪ የለም፡፡

ስለዚህ በእንስሳት ደህንነት ክርክር ውስጥ እነሱን ማካተት ተፈጥሯዊ ግዴታ ነው፡፡

መልካም ጊዜ!

በዘርፉ አዳዲስ ወቅታዊ አስተማሪ መረጃዎች እንዲደረስዎ ከዚህ በታች ያሉትን ሚዲያዎች ይቀላቀሉ ወይም አባል ይሁኑ፡፡
ዌብሳይት፡ https://wordpress.com/view/addisubihonegn.wordpress.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/semonegna
ፌስቡክ ግሩፕ፡ https://www.facebook.com/groups/514839721862656

ከወደዱት Like, Comment እና Share ማድረግዎን እንዳይረሱ፡፡